Monday, December 26, 2016

ከፋኝ አማራ ማነዉ ተልኮዉስ ምንድነዉ?


ከሰሞኑ በየሶሻል ሚዲያዉ ትግላችንን ተነጠቅን የአማራ ሕዝብ ትግል እዉቅና አጣ እያሉ ሲናገሩ የምንሰማቸዉ ሰዎች እነማን ናቸዉ አላማቸዉስ ምንድነዉ ለሚለዉ ጥያቄ መልስ ለማግኘት ከሰሞኑ የክትትል ምርመራ አድርገን ከዚህ በታች ያሰፈርነዉን መረጃ አግኝተናል።

 ሓራ ኢትዮጵያ

የከፋኝ አማራ ዋና ደጋፊነኝ የሚለዉ ሓራ ኢትዮጵያን በተመለከተ የሚቀጥለዉን ማስረጃ ልናገኝ ችለናል። በዉነተኛ ስሙ ሃይሌ አዳሙ አካሉ በመባል ይታወቃል፡ ጎንደር ዉስጥ ቢወለድም ከትግራይ ብሄረሰብ የወጣ ነዉ። ሃይሌ በራሱ አባባል ጂማ የከፍተኛ ትምህርት ከተማረ በሁዋላ ወደ ስዊደን ለፖስት ግራጁዌት ጥናት በወያኔ መንግስት ተልኮ ባሁኑ ወቅት ለPHDዉ እየስራ ያለ ሰዉ ነዉ። ሃይሌ በተለያየ ወቅት ስለማንነቱ ሲናገር አማራ ነኝ ሲል ተሰምትዋል እዉነቱ ግን ጎንደር በመወለዱ ካለዉ accent በስተቀር ያለቃዉ የበረከት ሲሞንን ያህል ነዉ አማራነቱ። ማንነቱን በተመለከተ አዎ ሃይሌ አማራ አደለም ድሩም ማጉም ትግሬ ነዉ። ተቃዋሚ ጎራ ገብቶ ለማመስ በሕወሓት በተሰጠዉ ተልኮ አማራ ሆኖ መቅርብ ጠቀሜታ አለዉ። ግንቦት 7 የአማራዉን ትግል ነጠቀ ፡ ግንቦት 7 የአማራ ሕዝብ ጠላት ነዉ ብሎ የአማራዉን ሕዝብ ከግንቦት 7 እና ከእሳት ለማጣላት እንዲመቸዉ ዛሬ አማራ ሆንዋል።

 በዶክተር ብርሃኑ ነጋ ላይ የጥላቻዉ ዘመቻ

በዶክተር ብርሃኑ ላይ ያለዉ ጥላቻ በጣም ስር የሰደደና የቆየ ነዉ። ቢያንስ አመት ይሆነዋል። ጉራጌ እንዴት የአማራ ተወካይ ይሆናል ፡ ግንቦት 7 በጎንደር በኩል ቢመጣ ጸጉር ልዋጭ ብሎ የጎንደር ሕዝብ ይፈጀዋል ሲልም አዲስ አደለም። ለጎንደር ሕዝብ ተቆርቅዋሪ በመምሰል የጎነደር ሕዝብ ሌሎችን እንደሚጠላ አርጎ የጎንደርን ሕዝብ ጭቃ የመቀባት ዘመቻ መሆኑ ግን ብዙዎች የገባቸዉ አይመስለኝም። በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች የሚኖሩ ቁጥራቸዉ ብዙ ጎንደሬዎች አሉ በኦሮምያ ብቻ በሚልየን የሚቆጠሩ ይኖራሉ ታዲያ ጎንደሬ አገሩ ሰዉ ሲመጣ ጸጉር ልዋጭ እያለ ይገላል ሲባሉ ጎንደሬን አኛ አገርህ መጥተን መኖር ካልቻልን አንተም ካገራችን ዉጣ ቢሉትስ? ሃይሌ ኢሄ ተስኖት አደለም አላማዉ እንደዚህ አይነት ስሜት ሌሎች ክልሎች ዉስጥ ተፈጥሮ ጎንደሬ እንዲመታ ነዉ። ሕወሓት ስልጣን ከያዘበት ቀን ጀምሮ አማራን ማስመታት ማዋረድ ማስጠላትን እንደ ስትራቴጂ የዞ የነበረ ዛሬም በዛዉ አላማ ጸንቶ የሚንቀሳቀስ ድርጅት ነዉ።

የሃይሌ የአማራ ጥላቻ ከሲሞን ልጅ ያማራ ጥላቻ ጋር ተመሳሳይ ነዉ። አማራ መስለህ አማራን ማስጠቃት፡ ማስወጋት፡ ማስመታት። አማራን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊነትንም ማስመታት። ሕወሓት የዶክተር ብርሃኑን ድርጅቱ ግንቦት 7ን በጣም ትፈራለች የምትፈራበት ዋናዉ ምክንያት ኢትዮጵያዊነትን ይዞ የሚንቀሳቀስ ድርጅት ስለሆነና ኢትዮጵያዊያንን ባንድ ኢትዮጵያዊነት በሚል ጥላ ስር የመሰበሰብ ችሎታ እንዳለዉ ስለምታቅ ነዉ። ኢትዮጵያዊነት ከሕዝብ ጭንቅላት ወጥቶ ሕዝብ በጎሳዊ አስተሳሰብ እንዲበከል የሕወሓት ምኞት ነዉ በተለይ ኢትዮጵያዊነቴን አለቅም ማንነቴ ኢትዮጵያዊነቴ ነዉ በሎ ያገሩን ድንበር እንደ ዘብ ሆኖ ይከላከል የነበረዉን ያማራን ሕዝብ በጎሳ ፖለቲካ መጠርነፍ የሕወሓት ምኞት ነበር።ዛሬ በ በረከት ስሞን ትዛዝ የሚሰራዉ ሃይሌ ያንን ተግባራዊ እያደረገ ነዉ። ዶክተር ብርሃኑ ነጋን የማቆሸሽ ዘመቻ የሕወሓት ተልኮ እንጂ ያማራ ሕዝብ አስተሳስብም ሆን ስነልቦናን አይወክልም። የአማራን ሕዝብ ሽፋን በማድረግ ሃይሌና ግብራበሮቹ የሚነዙት ፕሮፓጋንዳ ከበስተጀርባዉ ወያኔ እየመራዉ የጎንደር ታጋዮችን ለማስመታትና በወያኔ ላይ የመጣዉን ሓገር አቀፍ ተቃዉሞ ለማዳከም ከተሳካ ለማቆም በበረከት ሲሞን የተጠነሰሰ ሴራ ነዉ። ሃይሌ አዳሙ አካሉ የዛ ተልኮ አስፍጻሚና ከወያኔ የስለላ ድርጅት ጋ እጅና ጉዋንት ሆኖ የሚሰራ የሕወሓት አገልጋይ እንጂ ያማራ ትግል ደጋፊ አደለም። ስለዚ ግለሰብ ወደፊት ብዙ የምንለዉ ይኖራል ለጊዜዉ በዚህ እንለፈዉ።

 አባ መላ (ብርሃኑ ዳምጤ)

ወያኔዎች እንደ ኮንደም ተጠቅመዉ የወረወሩት አባ መላስ ለምን ይሄን የወያኔ ሴራ ፕሮሞት ያረጋል? እሱ የሚያገኘዉ ጥቅም ምንድነዉ? አባ መላ በተፈጥሮዉ ጥቅም እንጂ ህሊናዉ የሚመራዉ ሰዉ አደለም ጥቅም ለማገኘት ግን ምንም ነገር ከመናገርም ሆን ከማድረግ ወደ ሁላ የሚል ሰዉ አደለም። አባ መላ በቅናት የሚበገበግ ቂመኛ ነዉ። ፈሪም ነዉ።

ለመጀመርያ ጌዜ ከወያኔ ጎራ ወጥቻለሁ ብሎ ለኢሳት ኢንተርቪዉ ከሰጠ በሃላ ኢሳት ዉስጥ የተንታኝነት ስራ አገኛለሁ የሚል ተስፋ ነበረዉ ለስድስት ወር ጠብቆ አልሳካ ሲለዉ ዛሬ ከፋኝ አማራ ነን የሚሉት ሰዎች የሚሉት አይነት ነገረ ይዞ ወያኔዎች እግር ላይ ወድቆ ተመለሰ። ወያኔዎች ልክስክስነቱ ስላናደዳቸዉ ምንም ጥቅም እንዳያገኝ አረጉት እንድያዉም ይባስ ብለዉ እነ ኢዛናና ሺመልስን ማቅረብ ጀመሩ። አባ መላ ጥቅም ካላገኘሁ እንደገና ተቃዋሚ ለሁንና እድሌን ልሞክር ብሎ ለሁለተኛ ጌዜ ከች ቢልም ማንም ቦታ የሚሰጠዉ ሰዉ አጣ። እነ ሃይሌ ያማራ ሕዝብ ትግሉን ተነጠቀ በለዉ እምቡር እምቡር ማልት ሲጅምሩ አብዋራዉን ላጭስ በሚል መፈክር ተቀላቅሎ በፊትለፊት ሳይሆን በጋሮ ወያኔዎችን ማገልገል ጀመረ። ባየር ላይ ተንሳፎ እዝም እዚም እንደሌለ አድርጎ ራሱን ያቅረበዉ ባጋጣሚ ሳይሆን በስሌት ነዉ። ልቅምቃሚ ለመሰብሰብ ያመቻል። እንደ ወልደጊዮርጊስ አይነት የዋሆች ፍርፋሪ ነገር በመላክ ጊዜያዊ የሆነ ድል ያገኙ መስልዋቸዋል ያላወቁት ነገር ያባ መላ ሆድ ሲጎድል እነሱንም እንደሚበላቸዉ ነዉ።

አባ መላ ከፋኝ አማራን የሚያወድሰዉ አካሄዳቸዉ ትክክለኛ ነዉ ብሎ አደለም ኢሳትና ግንቦት 7ን ስለሚጠሉ ኢሳትን ብላክሜል በማረግ ካሳ እንዲከፈለዉ ነዉ። ኤርምያስ ለገሰ ወያኔ ነበር እሱ ኢሳት ላይ ተንታኝ ከሆነ እኔስ ለምን አልሆንም በሚል ቅናት እየበገነ ያል ሰዉ ነዉ። ኢሳትን የተቆጣጠሩት ጎንደሬዎች ናቸዉ ሲል የነበር ሰዉ ዛሬ የወልቃይትን የማንነት ጥያቄ ደጋፊ ነኝ በሎ ሲናገር ማመን ያስቸግራል። ስለ አባ መላ ብዙ መናገር ይቻላል እዚህ ሴራ ዉስጥ ያለዉ ሚና ግን ከራሱ ጥቅም ፈላጊነት ስለማያልፍ በዚሁ እንተወዉ።

 እርስቴ ተስፋዬ

በራስዋ አባባል ከወያኔ ጋ ጫካ ገብታ ስትዋጋ የነበረች አማራ መሆንዋን ስታቅ ሕወሓትን የተቀላቀለች ሴት ናት። ዛሬ አማራ መሆንዋን ስላወቀች ከፋኝ አማራን ደግፋለሁ ትላለች። ለመሆኑ እቺ ሴትዮ ማናት? በራስዋ አባባል ዛሬ ከፍተኛ አመራር ላይ ካለ የትግሬ ጀነራል ልጅ ወልዳለች መዉለድ በቻ ሳይሆን ዛሬም ከሰዉየዉ ጋ ያነበራትን ግንኙነት እንዳላቃረጥች አምናለች። ለግንቦት ሰባት ያላት ጥላቻ በወያኔ ፕሮፓጋንዳ ላይ የተመሰረተ ነዉ። ለመሳሌ ግንቦት ሰባት የሻብያ ተልኮ አስፈጻሚ ነዉ የሚለዉን የወያኔ ፕሮፖጋንዳ ቃል በቃል ትደጋግማለች እስዋ ከሻብያ ጋ ጎን ለጎን ተሰልፋ ኢትዮጵያዊያንን እንዳልገደለች። አማራዉ ሕዝብ ላይ ባነጣጠረ ትግራዊ ጎጥ ተደራጅታ ያማራዉን ሕዝብ ስትገድል ስታስገድል የነበርች ሴት ዛሬ ደሞ ባማራ ጎጥ እንደራጅና ሌላዉን እንፍጀዉ እያለች ነዉ። እርስቴ ከወያኔነት ወጥቻለሁ ትበል እንጂ ወያኔነት ከዉስጥዋ አለወጣም ዛሬም በዘር ተደራጅተን በዘር እንጠፋፋ እያለች ነዉ።

አዜብ ጎላ አንዴ ትግሬ ነሽ ወይስ አማራ ተብላ ስትጠየቅ በዘር አማራ ብሆንም በትግሬ ስነልቦና ስላደኩ ራሴን እንደ ትግሬ ነዉ የማየዉ ብላለች ርስቴም ከዛ የተለየች አደለችም። ርስቴ ብዙ ነገር አታቅም የእዉቀት እጥረት እንዳለባት ስትናገር ላዳመጣት ሁሉ ግልጽ ነዉ። ዉሸት ስትናገር እንካን ምን ያህል ርቀት መሄድ እንዳለባት አታቅም። ዝም ብላ መቀደድ ነዉ።

በጣም ሃብታም ከሆነ ቤተስብ ነዉ የተወለድኩት ሃብታም ከመሆናችን የተነሳ ከ Ford Motor Corporation ጋ ግንኝነት ነበርን ያ ብቻ አደለም ስንጋዝ እንኻ አዉሮፕላን ችርተር አርገን ነዉ።

እንደዚህ ይመቻል?

"Once a liar always a liar"
ይላሉ ፈረንጆች ርስቴም ያበሽታ የተጠናወታት ትመስላለች። ይሄ ተራ ዉሸት ነዉ ማንንም አይጎዳም እንድንታዘባት አርጎናል። ስለዚህ ከዋሸች ሰለሌላዉ አለመዋሸትዋን በምን እናቃለን? እዉነት እሳት ላይ ወጥታ እንደነገረችን ወያኔነትዋን ትታለች ወይስ ኢሳትን ተጠቅማ ወያኔነትን እንደተወች በማስመሰል ዛሬም ተቃዋሚዉን ጎራ ለማዳከም ከወያኔ ጋ እየሰራች ነዉ? በዙ ነገሮች ጥርጣሬ ዉስጥ እንድትገባ አርጋዋታል። ዛሬ ከልጅዋ አባትና ከሌሎች የሕወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋ ያላት ያላቅዋረጠ ግንኙነት በጣም አጠራጣሪ ነዉ።ርስቴን በተመለከተ ዛሬም ከወያኔ ጋ እየሰራች እንዳለች መረጃዎች ደርሰዉናል አስፈላጊ ሲሆን እንመለስበታለን።
Root13
በፓልቶክ ስምዋ root13 በመባል የምትታወቀዉ ሴት በቅንጅት ጊዜ ወያኔን ትደግፍ እንደነበር መደገፍ ብቻ ሳይሆን ወያኔዎች በአዲስ አበባ ሕዝብ ላይ ያረጉትን ጭፍጨፋ እልል እያለች በደስታ እንደ ደገፈች ስለምናቅ የስዋ ማንናት ለኛ አጠራጣሪ አደለም። በቅርቡ ወያኔን እቃወማለሁ ስትል በመስማታችን ተደስተን ነበረ ነገረ ግን የምትሰራዉን ስራ ስናይ ዛሬም ወያኔያዊ ትልኮ እንዳላት ለማወቅ ችለናል። እስዋና ርስቴን አንድ የሚያረጋቸዉ ሁለቱም ከትግሬ ተጋብተዉ ወልደዋል። ርስቴ ቢያንስ አደባባይ ወጥታ ማንነትዋን ተናግራለች። የአማራ ድምጽ ሬድዮ አንባቢ የሆነችዉ root13 የሚዲያ ሰዉ ሆና እንኻ ስምዋ ማን እንደሆነ አይታወቀም። ተፈጥሮዋ መጥፎ ልበ ጥቁር ሰይጣን ናት። የምትናገረዉ ብዙ ነገር ዉሸት ነዉ ሃይማኖትዋ ሳይቀር። ለብዙ ጌዜ የአፋር ብሔረሰብ ተወላጅና ሙስልም መሆንዋን ስትናገር ነበር ዛሬ አማራና የ ኦርቶዶክስ ተከታይ ነኝ ስትል ስመትን ገርሞናል። ለሻብያ ያላት ጥላቻም ወያኔያዊ ቅኝት አለዉ። ወያኔ ሕዝባችንን እየጨፈጨፈ ስለ ሻብያ መጥፎነት ሲያወሩላችሁ በጥርጣሬ ተመለከቱ። አባቴ የደርግ ወታደር ስለነበር አስመራ ነዉ ያደኩት ትላለች ትግሪኛ ስትናገር ተሰምታ ትግሬ አለመሆንዋን ለማስመስከር። ማንነታቸዉን የሚደብቁና ያልሆኑትን ነን ብለዉ የሚናገሩ ስዎቸን ተጠንቀቁ። ማንነታቸዉን የሚደብቁት ከበስተጀርባ ያልዉን ድብቅ አላማ ለመሸፈን ነዉ።
wakeupAmhara
ለፓልቶክ አዲስ ነኝ ብዙም ስለፖለቲካዉ አላቅም ሲል እወነትም አዲስ መስሎን ነበር ለመናገር አዲስ ይሆን እንጂ ለፓልቶክ አዲስ አይመስለንም። የሴት ድምጽ ያለዉ ፈላሻ ነዉ በራሱ አባባል። ከእስራኤል አግር መጥቶ ስያትል የምትባል ያሜሪካ ከተማ የሚኖር ሰዉ ነዉ። ግንቦት ስባትን ይቃወማል የሚሰጠዉ ምክንያት ከሃይሌ ብዙም አይርቅም ያው DNA ነዉ። ከምባታዎች ጉራጌዎች ያማራን ትግል አይመሩም ነዉ ባጭሩ። ወድያዉ አማራና ትግሬ DNAቸዉ አንድ ነዉ ይለናል። ትግሬዎች ከሌሎች የሚቀርቡን ወንድሞቻችን ናቸዉ ለማለት ይመስላል። የሄን የሚነግረን ዘረኛ አይሁዶች ፈላሻዎች የኛ ዘር አይደሉም አፍሪካዎች ናቸዉ ለማለት በተዘጋጀ የ DNA ጥናት ላይ ተመርኩዞ ነዉ። ምን የዘር ስር ቆጠራ አስገባዉ እኛ እኮ ትግሬዎች ወንድሞቻችን አደሉም ብለን አናቅም፡ ጠባችን ክሕወሓት እንጂ ከትግሬዎች አልነበርም አሁንም አደለም። ኢትዮጵያዊነቱ አጠራጣሪ ሰዉ ነዉ ቢያንስ የኢትዮጵያዊነት ስነልቦና የለዉም። ምክንያቱን መገምት ከባድ አደለም ለዛሬዉ ግን እዚህ ላይ እንደመድማለን።

No comments:

Post a Comment